
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ በዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት አብሮ መስራት ጀመሩ
Posted on: 23 Jul, 2025
የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ዳይናሚክማይክሮፋይናንስ ተቋም (አ.ማ) እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ክፍያ ሰነድ አውጪ የሆነው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎት (አ.ማ) መካከል ወሳኝ የስትራቴጂክ ትብብር ተፈርሟል።
ይህ ትብብር አስፈላጊውን መስፈርቶች አሟልቶበብሔራዊ ባንክ የፀደቀ ሲሆን በዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ዋና መሥሪያ ቤት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተከናውኗል ::
ይህም የኢትዮጵያን የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ በፈጠራ እና በስትራቴጂክ ውህደት ለማዘመን የተደረገ የጋራ ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል ።
የማይክሮፋይናንስ አገልግሎቶችን በዲጂታል መልክ ማቅረብ እና በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግ ደንበኞች ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በስልካቸው ብቻ የመሚያገኙት ምቹ የፋይናንስ አገልግሎቶች ለማስፋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ተቋማቱ የጋራ የሞባይል መተግበሪያ(ኮ-ብራንድ) እና USSD አስጀምረዋል።
ይህም የተለያዩ የዲጂታል ቁጠባ አገልግሎቶች፣, ቁጠባ- ላይ የተመሰረተ ብድር, የደሞዝ መዳረሻ ብድር ለአነስተኛ እና መካከለኛኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አገልግሎቶች , የእርሻ ብድር, እናበርካታ ‹አሁን ይግዙ፣ በኋላ ይክፈሉ› አማራጮችን ጨምሮየተለያዩ አገልግሎቶችን ያቀርባል።
እነዚህ አገልግሎቶች ለተለያዩ የገቢ ደረጃዎች እና የኢኮኖሚዘርፎች የሚገኙ ደንበኞች የዕለት ተዕለት የፋይናንስ ፍላጎቶችንለማሟላት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል።
Comments (0)
Post Your Comment